የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ በመደበኛ እና በCMP ፕሮግራም በጀት ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የውሀ ማጣሪያ ቦትል፣ ሎት 2. የተሸከርካሪ መለዋወጫ፣ ሎት 3. የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ሎት 4. የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ኤሌክትሮኒክስ/ እና ሎት 5. ብስክሌትና የብስክሌት ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ሎት 1፣ 2 እና ሎት 5 ለተዘረዘሩት 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ሎት 3 እና ሎት 4 ለተዘረዘሩት 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ሕጋዊ ማህተም፤ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግሥት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፅም ይሆናል፡፡ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 01 32/ 058 220 10 87 ዘወትር በሥራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ/ ቀበሌ 07 ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት