ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
169

የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን  በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ሕጋዊና ብቃት ካላቸው በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት1.የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2. ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት3. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት4. የመኪና እቃዎችና ታፕሰሪ ሥራ፣ ሎት5. የፈርኒቸር እና ተዛማጅ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ  የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻው ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 05 የገቢዎችና ጉምሩክ ቢሮ ከነበረው G+4 ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 412 በመምጣት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ተጫራቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የግዥ መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒዩ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት  በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት ንብረቱን የሚረከበው በተጠቃሚዎች የጥራት ትክክለኛነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ የውል አፈጻጸም ዋስትና /ፐርፎርማንስ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱም ሆነ ከተጠየቀው እስፔስፊኬሽን ውጭ ምንም አይነት ጽሑፍ ማስፈር የለባቸውም፡፡
  8. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 304 ከቀኑ 4፡15 በግልጽ ይከፈታል፡፡ በ22ኛው ቀን  የሥራ ቀን ካልሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 00 82 ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here