በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 07 መሰታ የገበያ ማዕከል አ/ማ ለሚያስገነበዉ B+G+8 እና ከዚያ በላይ ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ለሁሉም የስነ-ህንፃ እና ምህንድስና አማካሪዎች ምድብ ሁለት (2) እና ከዚያ በላይ በህንፃው ዘርፍ ለተሰማሩ ፈቃዳቸው ለ2016 ዓ.ም የታደሰ እንዲሁም የባለሙያ ብቃት እና ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳትፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
- የመሰታ ገበያ ማዕከል ለB+G+8 እና ከዚያ በላይ ቅይጥ አገልግሎት የሚውል ሕንፃው በአሁኑ ጊዜ እየተገነባ ሲሆን የመዋቅር ሥራው እስከ አንደኛ ፎቅ እስላቭ ድረስ ተጠናቅቋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ተጨማሪ ወለሎችን የመጨመር እድልን ግምት ውስጥ በማስገባት ዲዛይኑን ማሻሻል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ፍላጎት ያላቸው ብቁ ተጫራች ለመሰታ ገበያ ማዕከል የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በአቢሲኒያ ባንክ በሂሳብ ቁጥር M 8098 እና በንብ ባንክ 9543 ክፍሎ በመቅርብ የመጫረቻ ሰነዱን በባሕር ዳር ከተማ በላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ በቀበሌ 07 በዊዝደም ታወር ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮ መውሰድ እና መጫረት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው በሰም የታሸጉ ፓስታ (አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ቅጂ) ለሁለቱም (ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል/ ሰነዶችን በተናጠል (ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን ለየብቻ) ከጨረታ ዋስትና ከጠቅላላው የጨረታ መጠን አንድ በመቶ (ተ.እ.ታን) ጨምሮ በተለየ ኢንቨሎፕ በማሸግ በማህበሩ ቢሮ ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 02/2016 ዓ.ም ከእሁድ ቀን ውጭ በሌሎች 14 ተከታታይ ቀናት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተመረጠው ተጫራች ከጠቅላላ የጨረታ መጠን (ተ.እ.ታን) ጨምሮ አስር በመቶውን ለአፈጻጸም ዋስትና ማስጠበቅ ይጠበቅበታል፡፡
- ዲዛይን ማሻሻያ ሥራው ሥራ ውል ከሚያዝበት ጊዜ አንስቶ ቢበዛ በ60 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ሚያዚያ 03/2016 ዓ.ም 8፡30 ቢሮ በሚገኘው የመሰታ ገበያ ማእከል ይከፈታል፡፡
- አክሲዩኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 09 18 80 01 34 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡