ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
152

በደቡብ ጎንደር ዞን የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገ/ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት አቅርቦቶችን ማለትም. የውሃ መገጣጠሚያ እቃዎች እና የውሃ ቆጣሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ  ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ  የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር  አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፈኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ  ሰነዱን የማይመለስ 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከገ/ግ//ፋ/ን/አስ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር  8 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲ.ፒ.ኦ/ ማስያዝ  አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጂዎች በጥንቃቄ  በታሸገ  ፖስታ ለመካነ ኢየሱስ ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ  በ15 ተከታታይ  ቀናት  ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ቀን 11፡00 ጨረታው  ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት በቢሮ ቁጥር  8 በ16ተኛው ቀን  4፡00 ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ  ካገኘ ጨረታውን  በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ  መብቱ  የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 447 03 02/ 09 18 18 84 82 /09 46 12 49 45 በመደወል ማግኘት  ይችላሉ፡፡

የመካነ ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ውሃ አገ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here