በምስራቅ ጎጃም ዞን በሉማሜ ከተማ አስተዳደር የሉማሜ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የተለያዩ የውሃ እቃዎችን /ቆጣሪ፣ ቧንቧና መገጣጠሚያ/ በግልጽ ጨረታ በጋዜጣ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸው ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከሚገዙት የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 150.00 / አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ /በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጁዎች ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤቱ በገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ16/07/2016 ዓ.ም እስከ 30/07/2016 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 02 በ30/07/2016 ዓ.ም የጨረታ ሳጥኑ 3፡00 ላይ ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 772 04 65/ 0645 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የጨረታውን ሃያ አምስት በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከተጫራቾች ተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር /withhold tax/ ከግዥው ዋጋ ላይ የሚቀነስ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት ውል መያዝ አለበት፡፡
- አሸናፊው ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡:
- አሸናፊው ያሸነፈውን እቃ ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ነው፡፡