የድልድይ ግንባታ ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ

0
162

የጨረታ ቁጥር ET-ANRSBOA-382849-CW-RFQ

በአብክመ ግብርና ቢሮ በስደተኞች ተጽእኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀክት /DRDIP II/ በዓለም ባንክ የበጀት ድጋፍ  በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 04 አነስተኛ ድልድይ ግንባታ በጠቅላላ ተቋራጭ ወይም በመንገድ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ አምስት እና በላይ /GC/RC-5 and above/ የሆኑ ተቋራጮችን በዋጋ ማወዳደሪያ ግዥ ዘዴ /Request for Quotations/RFQ/ አወዳድሮ/ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ለዚህ ሥራ ማስፈጸሚያ የተገኘው በጀት ከዓለም ባንክ ድጋፍ በመሆኑ የጨረታ ግምገማ ሥርዓቱ በክልሉ የግዥ መመሪያ ሳይሆን የአገሪቱ መንግሥት በተፈራረመበት የዓለም ባንክ /የፕሮግራሙ የግዥ መመሪያ/ አፈጻጸም መሰረት በመሆኑ የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መገምገሚያ መሥፈርት መሰረት የቴክኒክ ግምገማ በመፈጸም የቴክኒክ መስፈርቱን ካሟሉ ተወዳዳሪዎች መካከል የዋጋ ንጽጽር ተደርጎ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት የሚመረጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ደረጃ ቢሲ/ጂሲ-5 እና በላይ ሆኖ በዘመኑ የታደሰና በዘርፋ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን እና የግብር ከፋይነት መለያ /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ከኦርጅናል ሰነዳቸው ጋር አያየዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከፕሮጀክቱ ገ/ያዥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም መጋቢት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ሥርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሰረት የአንዱን የነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ ቴክኒካል ፋይናንሻል ለየብቻ  በማሸግ ሁለቱንም በሌላ ትልቅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት ከተለየ በኋላ ለግንባታ ሥራው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና አስር በመቶ እና መሥሪያ ቤቱ ለሚከፍለው ሃያ በመቶ ቅድመ ክፍያ ዋስትና በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ጋራንቲ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  10. የጨረታ ግምገማ ሥርዓት በዓለም ባንክ የግዥ አፈጻጸም መመሪያ በመሆኑ ሁሉም ተወዳዳሪዎች በእኩል መስፈርት የሚገመገሙ ሲሆን በውድድር ወቅት ለተወሰኑ ተጫራቾች ምንም አይነት ልዩ ድጋፍ አይሰጥም፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አብክመ ግብርና ቢሮ ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ሚያዚያ 01/2016 ዓ.ም ቀን 4፡00 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል /ዝግ/ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የማይገኙ ከሆኑ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 64 31 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 55 21 በመላክ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብከመ ግብርና ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here