በአብክመ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሻሁራ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴ/መ/ቤቶች አግልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 2. የጽሕፈት መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሥሪያ ቤት የገቢ ደረሰኝ /መሂ-1 /ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-4 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከሻሁራ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በሻሁራ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ16/07/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 30/07/2016 ዓ.ም አየር ላይ ይውላል በ16ኛው ማለትም 01/08/2016 ዓ.ም የጨረታ ሳጥኑ አስከ ሚታሸግበት አስከ 4፡00 የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሻሁራ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በመመሪያው መሰረት የጨረታ አከፋፈት ስርዓት ተገዥ ሆነው በሻሁራ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የጨረታ አሸናፊው ላይ ሃያ በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡