የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ

0
171

የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በኦሮሚያ ክልል  አርሲ ዞን ይገኛል:: በብሔራዊ ፓርክነት ተከልሎ ስያሜውን ያገኘው በ2011 እ.አ.አ ሲሆን ጠቅላላ ስፋቱም 10, 876 ኪሎ ሜትር ስከዌር ተለክቷል:: ፓርኩን በበላይነት የሚቆጣጠረው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ነው::

ብሄራዊ ፓርኩ በደጋማ ቦታዎች የሚገኙትን የአርሲ ተራራዎችን ያጠቃልላል:: ተራሮቹ ከፓርኩ ክልል ሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫን ይሸፍናሉ:: ከተራሮቹ መካከል የጭላሎ ተራራ፣ ደራ ዲልፋቀር፣ የጋለማ ተራራ፣ የካካ ተራራ እና ሁንኮሎ ይገኙበታል:: የጭላሎ ተራ 4036 ሜትር ከፍታ ተለክቷል::

በፓርኩ ክልል ሀይቆች እና ወንዞች ይገኙበታል:: በሰሜናዊ ተዳፋት ያሉት ወደ አዋሽ ወንዝ፣ በደቡብ ተዳፋት ያሉቱ የዋቢሽበሌ ወንዝን ይቀላቀላሉ::

ፓርኩ በሦስት መልክዓምድራዊ አቀማመጥ የተከፈለ ነው:: በዚሁ መሠረትም ሦስት የዕፅዋት ስነ ምህዳሮች ተለይተውበታል:: ዝቅተኛው ከ2843 እስከ 3756 ሜትር ከፍታ የማይረግፍ ደን፤ ከ3202 እስከ 3985 ሜትር ከፍታ ያለው ቁጥቋጦዎች የተደባለቁበት ደን፣ ሦስተኛው ከ35 76 እስከ 4008 ሜትር ከፍታ ሳር እና ቁጥቋጦዎች፣ ጅብራ  የሚበዛበት ነው::

በፓርኩ ከሚገኙ የዱር እንስሳት የተራራ ኒያላ፣ ተኩላ፣ ጥንቸል እና የደጋ አይጦች፣ ቀበሮ፣ ይጠቀሳሉ:: ጠቅለል ሲል በፓርኩ ክልል በ2018 እ.አ.አ በሁለት ወቅቶች በተደረገ ጥናት 18 አጥቢ የእንስሳት ዝርያዎች ተመዝግበዋል::

ምንጭ፡- iiab   /KIWIX/ WIKIPEDIA. FONDATON SEGRE. ORG.REPOSITORY. JU.EDU. ድረ ገፆችን ተጠቅመናል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here