የሊዝ የቦታ ጨረታ ማስታወቂያ

0
139

በደቡብ ጎንደር ዞን በታች ጋይንት ወረዳ በአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2016 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ የሚገኙትን የመኖሪያ፣ የድርጅትና የመጋዘን ቦታዎች በአዋጅ ቁጥር 721/2004 በደንብ ቁጥር 103/2004 አንቀጽ 13/2 በመመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀጽ 17 በሚያዘው መሰረት አጫርቶ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ አርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/  ገዝታችሁ መጫረት ትችላላችሁ፡፡ የጨረታ ፖስታውን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ07/05/2016 ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይቆያል፡፡ በ10ኛው ቀን 18/08/2016 ዓ/ም እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት የምትችሉ እና ሳጥኑ በዚሁ ቀን በ11፡30 ላይ ይታሽጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በ11ኛው የሥራ ቀን 21/08/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ አርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የሚከፈት ሲሆን በ4፡00 ላይ ተጫራችም ሆኑ ሕጋዊ ወኪል ባይገኝም ፖስታው ይከፈታል፡፡ ተቋሙ ጨረታውን ካልተስማማበት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳስባለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 49 98 89 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here