በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን በ2016 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ አገልግሎት የሚውሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እና ጎማ በነጠላ ዋጋ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል:: ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ይኖርባቸዋል፡-
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ክሪላንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የግዥ ኤጄንሲ የምዝገባ ወረቀት (የአቅራቢነት) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቅጣት የሌለባቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል::
- ከ200,000.00/ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሚጫረቱ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ በደንብ ሊነበብ የሚችል ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አብክመ ፖሊስ ኮሚሽን 1ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 128 መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማ እና የድርጅቱን ማህተም ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ ሆኖ በአንድ ፖስታ በማጠቃለል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማዘጋጀት ከዋናው ሰነድ ጋር በፓስታ በማሸግ መስገባት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል:: ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል::
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በኦርጅናል ሰነዱ ላይ ብቻ በእያንዳንዱ ላይ ቫትን ያጠቃለለ ዋጋ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ይፋ በሚደረገው ውጤት ቅሬታ ካላቸው በ7 ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን የማቅረብ መብት አላቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ ፍሉድ ተጠቅሞ በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ውጪ ይሆናል::