የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትህ ቢሮ ለ2016 ዓ.ም ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 2. ፈርኒቸር እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ተጫራቾች ሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው::
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤ ነገር ግን ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.ዐዐ/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በአብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 /የገንዘብ ያዥ ቢሮ/ መግዛት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን ዋጋ ለኤሌክትሮኒክስ ሎት 1. 18,000.00/ አስራ ስምንት ሺህ ብር/ እና ለፈርኒቸር ሎት 2. 5,000.00/አምስት ሺህ ብር/፣ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ /ታብሌት/ እቃዎች 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ ሎት 2. ለፈርኒቸር እቃዎች 7,000.00/ ሰባት ሺህ ብር/በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ/ፖስታ/ በማድረግ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ቴክኒኩን ለብቻ በአንድ ፖስታ በማሸግና ፋይናንሽያሉን ለብቻ በሌላ ፖስታ በማሸግ እንድታስገቡ እያሣሰብን ሌሎች እቃዎችን ግን እንደተለመደው በታሸገ ኢንቨሎፕ/ፖስታ/ በማድረግ በመሥሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ7/08/2ዐ16 እስከ 21/08/2ዐ16 ዓ.ም ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አብክመ ፍትህ ቢሮ መሥሪያ ቤት ቢሮ 04 በ16ተኛው ቀን በ 22/08/2016ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል:: የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- የሚገዙ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል::
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመሥሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል ማግኘት ይቻላል::