ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
129

የጨረታ ቁጥር NCB WWC 12/2016

ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለዓባይ አዲስ ልደት መስኖ ልማት ፕሮጀክት ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ በንዑስ ተቋራጭ GC ወይም WC የሥራ ፍቃድ ከደረጃ 7 ጀምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ሕጋዊ  ድርጅቶች ሥራውን ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የንዑስ ተቋራጮች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ ምዝገባ ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተቋራጮች የግንባታ ሥራውን ውል ወስደው ሳይት ርክክብ ካደረጉ በኋላ በ90 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስረከብ አለባቸው።
  3. ተቋራጮች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን በውሃ ሥራዎች ኮርፓሬሽን ስም የተሠራ ሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቁ የሚከፈል /Unconditional performance bond/ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ለ120 ቀናት እና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለባቸው:: አሸናፊው ከተለየ በኋላ በአሸናፊነት ላልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸናፊው ጋር ውል ከተያዘ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 ተከታታይ ቀናት ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ቢሮ 1ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል በኮርፖሬሽኑ አካውንት ቁጥር 1000 265 163 223 በማስገባት የክፍያ ማረጋገጫ ማስረጃ ይዞ በማቅረብ ወይም ቀጥታ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተቋራጮች የመወዳደሪያ ዓይነቶች ማለትም የቴክኒክና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመለየት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 20 ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 33 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ 8:30 ተቋራጮች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ቢሮ ህንጻ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ባይገኙም ጨረታው በግዥ ኮሚቴ አማካኝነት ስለሚከፈት ተጫራቾች ከውድድሩ አይታገዱም ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ስነ ስርዓቱ ለሚወሰዱ ማንኛውም ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  7. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ ወይም የኮርፖሬሽኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የተጫረተበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማሠራት፣ ማስያዝ እና በአካል ቀርቦ ከኮርፓሬሽኑ ጋር የውል ስምምነት መያዝ አለበት፡፡
  9. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፤ ለወደፊትም ኮርፖሬሽኑ በሚያወጣው ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
  10. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በአካባቢው ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡ ለበለጠ መረጃ በፖ.ሳ.ቁ 106፣ ስ.ቁ 058 222 14 79፣ ፋክስ 058 222 13 35 አድራሻ ባሕር ዳር ቀበሌ 14 ከአዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት ይገኛል፡፡

 

የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here