ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
150

ቁጥር ግጨ 03/2016

በአብክመ ገንዘብ ቢሮ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም፡- ጀነሬተር፣ ሊፍት፣ ፓወር ሞጁል (Power Module)፣ ስታቲክ ስዊች ሞጁል (Static Switch Module)፣ የጉዞ ፖርሳዎችን፣ የብስክሌት ጎማዎችን፣ አጀንዳዎችን እና የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ፣የሚቀርበው እቃ የግዥው መጠን  ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ  የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ በማሸግ እና ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ   ቁጥር 108 በመቅረብ የማይመለስ  00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር ) በመክፈል  ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን በመሙላት የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት / ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ4፡00 ይዘጋና በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው የአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ. ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ይከፈታል፤ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፤ የመጫረቻ ሰነዱ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ ለቢሯችን  ቢደርስ የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ አገልግሎት አይነት የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ድረስ እቃውን /አገልግሎቱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  7. ለእቃዎቹ የቀረቡት ስፔሲፊኬሽኖች፣ መመሪያዎችና የውል ቃሎች ከጨረታው ሰነድ ጋር አባሪ ሆነው የቀረቡ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  8. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡
  9. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here