ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
168

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባህል ቱሪዝም ቢሮ ለ2016 በካፒታል በጀት በማ/ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ የኖራ ማቃጠያ፣ መጋዝን፣ ላቦራቶሪ፣ የጥበቃ ቤት፣ መፀዳጃ ቤት እና አጥር የያዘ ፕሮጀክት ግንባታ ግዥ ደረጃ ሰባት እና በላይ በግልፅ ጨረታ አውዳድሮ በጠቅላላ ዋጋ (ሎት) ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆንናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የብቃት ማረጋገጫ፣ በዘርፍ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የእጅ ዋጋ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከግ/ፋይ/ንብ/አስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 213 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አስበው አንድ ነጥብ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመሥሪያ ቤታችን ገንዘብ ያዥ መ/ሂ1  ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋጋ ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ባህል ቱሪዝም ቢሮ በግ/ፋይ/ንብ/አስ ደጋፊ የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 213 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት እና በ22ኛው ቀን 8፡:00 ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ ደጋፊ የሥራ ሂደት ክፍል በቢሮ ቁጥር 213 በ22ኛው ቀን በ8፡00  ታሽጎ በዚያው ቀን በ8፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎች ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉልም፡፡
  10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቅድም ካለው ፓራፍ ይደረግበት፡፡
  12. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር (ሎት) ድምር ይሆናል፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 213 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 42 70 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 58 64 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝም ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here