ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
136

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የተለያዩ ያገለገሉ የግንባታ እቃዎች፣ ያገለገሉ የማሽነሪ ተሸከርካሪ እና የመደበኛ የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን ባሕር ዳር በሚገኙ መጋዝኖች ማለትም ዋናው ቢሮ፣ ቀበሌ 08 እና ባህር ዳር ግን/ግ/ማ/ማዕከል ንብረት ክፍል በሚገኙ መጋዝኖች ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ዕቃዎቹ ያሉበትን ሁኔታና አይነታቸውን በአካል ተገኝቶ መመልከት ይቻላል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ማንኛውንም ዕቃዎች ለመግዛት የሚፈልጉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች፤ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች፤ የመንግሥት ተቋማት እና ፋብሪካዎች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት  ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው አስፖልት መንገድ 600 ሜትር ገባ ብሎ ቢሮ ቁጥር 009 የማይመለስ 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡ የዕቃዎችን አይነትና መጠን የያዘ ዝርዝር መረጃ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ተካቷል፡፡

  1. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) 8፡00 ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 8፡00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 009 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን 8፡30 ድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 009 ይከፈታል፡፡
  4. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  5. በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ አካቶ ማቅረብ የሚገባው የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ አስር በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለበት፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ መብለጥ የለበትም፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊው ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አስር በመቶ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና /ፕርፎርማንስ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ይችላል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  9. በጨረታ ሠነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ፊርማና ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
  10. በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊዎች ንብረቱን በራሳቸው ወጪ ከቦታው ድረስ በመሄድ ቆጥረው ወይም መዝነው ይረከባሉ፡፡
  12. አሸናፊዎች ውለታ ከፈረሙ በኋላ የአሸነፉበትን የእቃ ዋጋ ጠቅላላ ከቫት ጋር ንብረቱን ከመጫናቸው በፊት ቅድሚያ ለድርጅቱ ገቢ ያደርጋሉ፡፡
  13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 218 10 04 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here