ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
124

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክላስተር አንድ ወረዳ ፍርድ ቤቶች ማለትም ማቻከል፣ ደብረ ኤልያስና ስናን ወረዳ ፍርድ ቤቶች በ2016 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የህትመት ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መሥሪያ ቤቱ ባወጣው በግልጽ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅርብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ኮፒውን እና የዋጋ መሙያቸውን ኦርጅናል በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. የሰነዱን ዝርዝር መግለጫ ከምስ/ጎ/ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 100 ድረስ በመምጣት ሰነድ በነጻ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ ማስረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 771 11 28 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ጠቅላላ ዋጋ ከዜሮ ነጥብ አምስት እስከ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ በሁኔታው ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ሀሳቡን በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ምስ/ጎ/ዞን/ከፍ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 100 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ ጨረታው የሚከፈተው በእለቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. መሥሪያ ቤቱ አሸናፊውን ድርጅት የሚለየው በሎት (በጠቅላላ ድምር) ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  12. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቻውን ማስፈር ይጠበቅባቸዋል፡፡
  13. ተጫራቾች የሚሰጧቸውን የመጫረቻ ዋጋዎች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ያልተመሰረቱ መሆን አለባቸው፡፡
  14. መሥሪያ ቤቱ ከተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቹ የሞላውን ዋጋ ሳይለወጥ ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች ምስ/ጎ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
  16. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የማቻከል ወረዳ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here