በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፍትህ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት በ2016 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2. ቋሚ እና ቋሚ አላቂ የኤልክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3. የኤሌክትሪክ ኬብል ፣ ሎት 4 የውሃ እቃ፣ ሎት 5. የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ፈሪኒቸር የውጭ፣ ሎት 6. የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ፈሪኒቸር ያገር ውስጥ፣ ሎት 7. የመኪና ጎማ ከነካላማዳሪው፣ ሎት 8. የሞተር ብስክሌት ጎማ ከነካላማዳሪው እና እቃ፣ ሎት 9. ብስክሌትና የብስክሌት ጎማ ከነካላማዳሪው እና ሎት 10. የፕላስቲክ ወንበር፣ ጥቅል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑ የታደሰና ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የግዥ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወቀረት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣታፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ከነቫት ከጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መመሪያው በየሎቱ የተጠቀሰውን የብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶችን ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ20/09/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ቢሆን በቀጣዩ ባለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ የፍትህ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝመ ብቱ የተጠበቀነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 01 22/ 058 226 01 31/ 058 890 91 09/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡