የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 2. ፈርኒቸር በአንድ ጊዜ የሚቀርብ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን /አገልግሎቶችን/ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ / ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከግንቦት 05/2016 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዩቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዩቱ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከግንቦት 05/2016 እስከ ግንቦት 20/2016 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ግንቦት 20/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡