የኢንቨስትመንት የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
204

የሰሜን ወሎ ዞን የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት የሊዝ ጨረታ ኮሜቴ የከተማ ቦታን በሊዝ ሰለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ቁጥር ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከግንቦት 05 /2016 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ ማወቅ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በመሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

  1. የጨረታው ዙር፡- 1ኛ ዙር የ2016 ዓ.ም
  2. የጨረታው ዓይነት፡- መደበኛ
  3. ቦታው የሚገኝበት አድራሻ
    • መርሳ ከተማ 01 ቀበሌ ከሮዝ ካፌ ጎን 127.5 ካ.ሜ (ኮድ -1) ለኢንቨስትመንት አገ/ት G+4 እና ከዚያ በላይ፡፡
    • ቀበሌ 02 ከ እቋር አበራ ቤት ጀርባ 212 ካ.ሜ (ኮድ -2) ለኢንቨስትመንት አዝ/ት G+4 እና ከዚያ በላይ፡፡
    • ቀበሌ 03 ዋጩ 2856 ካ.ሜ (ኮድ -3) መዋዕለ ህፃናት ት/ቤት፡፡
  4. ቦታው ከማንኛውም ክርክር ነፃ ነው፡፡
  5. የቦታው ደረጃ (ሀ እና ለ) 1ኛ ደረጃ ሲሆን (በ 3.3) የተገለፀዉ የቦታዉ አጠቃቀም S11፡፡
  6. የጨረታው መነሻ የሊዝ ዋጋ ለ1 ካሬ 500 (አምስት መቶ ብር የኢትዮጲያ ብር ብቻ)፡፡
  7. የሚፈለገው አነስተኛ የቅድሚያ ክፍያ መጠን አጠቃላይ የቦታውን ዋጋ ሃያ በመቶ ይሆናል፡፡
  8. የቀሪ ክፍያ ማጠናቀቂያ መጀመሪያ ክፍያ ከተከፈለበት ከ2 ዓመት የፎይታ ጊዜ በኋላ ጀምሮ እሰከ ሊዝ ዘመኑ 40 አመት (አርባ) ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ እንደተገለፀለት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ዋጋ ከሃያ በመቶ ያላነስ ቅድሚያ ክፍያ ወይም በቴክኒካል ፕሮፖዛሉ ላይ የገለፀውን ቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም ውል ይፈፀማል፡፡ በተጠቀሰው ቀን በሚሰጠው ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ 2ተኛ የወጣው አንደኛ የወጣው ዋጋ በመስጠት መውሰድ ከፈለገ ይሰጠዋል፡፡
  10. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የተጫረተበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማብዛት የሚገኘውን ውጤት አምስት በመቶ ያላነሰ በኦርጅናል ፖስታ ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  11. ተጫራቹ የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በማድረግ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ታሽጎ በጽሁፍ ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡
  12. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የቦታ ዋጋ በፊደልና በአሀዝ መሙላት ይኖርበታል፡፡ በፊደልና በአሀዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፌደል የተፃፈው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
  13. አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይቻልም ገዝቶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  14. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚጀምርበት ጊዜ ከግንቦት 05/2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም በአስር የሥራ ቀናት ከቀኑ እስከ አስራ አንድ ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  15. በሰነድ ማሳሰቢያው ሀሳብ ላይ በፊደልና በአሀዝ የተፃፈው ሥርዝ ድልዝና የሚያምታታ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  16. የጨረታው የሰነድ ሽያጭ የሚያልቅበት ግንቦት 16/2016 ዓ.ም በ11፡00 ሲሆን ከዚህ ሰዓት ዉጪ የጨረታ ፖስታ የማንቀበል መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
  17. ሰነዱን በመሬት ልማት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት) በመምጣት በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
  18. ቦታውን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በማንኛውም የሥራ ስዓት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  19. ጨረታው የሚከፈተው በግንቦት 19/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 በመርሳ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  20. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 033 333 00 68 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
  21. መሥሪያ ቤቱ በጨረታው ካልተስማማ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የመርሳ ከተማ አስ/ር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here