በግብርና ኢንቨስትመንት የሚለማ መሬትን ለሚፈልጉ በውድድር ለማሰተላለፍ የወጣ የውድድር ማስታወቂያ:: በውድድሩ መሳተፍ ለምትፈልጉ አልሚ ባለሀብቶች በሙሉ በአብክመ መሬት ቢሮ 2016/2017 የምርት ዘመን በግብርና ኢንቨስትመንት ሰብል ልማት የሚዉሉ የኢንቨስትመንት መሬቶችን በውድድር ለአልሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፤ በመሆኑም መወዳደር የምትፈልጉ አልሚ ባለሀብቶች የሰነዱን ዝርዝር መረጃ መሬት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 18 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በሥራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዝርዝር ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::