በኢትዮጵያ በመንግሥቱ እና ግርማሜ ንዋይ ካደረጉት ያልተሳካ መፈንቅለ መንግሥት ወዲህ ሁለት መፈንቅለ መንግሥቶች ተደርገዋል። ንጉሡ ከመንበራቸው የተነሱት ደርግ በፈፀመው መፈንቅለ መንግሥት መሆኑ ይታወሳል። ከዚያ በኋላ ነበር በፕሬዚደንት መንግሥቱ ላይ ያልተሳካው መፈንቅለ መንግሥት በግንቦት 8 ቀን 1981 ዓ.ም ተሞክሮባቸው ነበር። በወቅቱ ፕሬዝደንቱ ወደ ምስራቅ ጀርመን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለመፈራረም ለመብረር በዝግጅት ላይ ነበሩ። ነገር ግን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች አውሮፕላኑ ሲነሳ እንዲመታ ታስቦ ነገር ግን እንዲከሽፍ ሆኗል። እነዚህም በርካታ የጦር መኮንኖች እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን ልብ ይሏል።
ምንጭ፡-ፍቅረሥላሴ ደስታ አብዮቱ እና ትዝታየ