ለዓዕምሮ ጤና ቀውስ የሚዳርገው

0
202

ከወንድሞቻቸው እና ከእህቶቻቸው በበለጠ መኖሪያ ቤታቸው የተመሰቃቀለ፣ በወጉ ያልተደራጀ እንደሆነ አድርገው የሚመለከቱ ታዳጊ ወጣቶች በጉልምስና ዕድሜያቸው ለዓዕምሮ ጤና ቀውስ ሊዳረጉ እንደሚችሉ ሳይንስ ዴይሊ ድረገጽ አስነብቧል::

በእንግሊዝ ዮርክ ዩኒቨርስቲ የስነ ልቦና ኘሮፌሰሯ ሶፊያ ቮን ስቱም በታዳጊነታቸው ከወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው የበለጠ ቤታቸው የተዘበራረቀ፣ የተበታተነ አድርገው የሚመለከቱ በጉልምስና ዕድሜያቸው የዓዕምሮ ጤና እና የባህሪ ችግሮች እንደሚታይባቸው ባደረጉት ጥናት አረጋግጠዋል::

ለጥናትና ምርምራቸው 4,732 ከወንድማማች እና እህትማማቾች የተሠበሰበ መረጃን ፕሮፌሰሯ ተጠቅመዋል።

ከዘጠኝ እስከ 16 ዓመት ዕድሜ የሆናቸው- በቤታቸው ሁከት፣ አለመረጋጋት፣ መዘበራረቅ አለ ብለው የመለሱት እያደር ለዓዕምሮ ቀውስ ሊዳረጉ እንደሚችሉ ነው በጥናቱ የተመላከተው:: ምነው ቢሉ ቤቱ በብጥብጥ፣ ባለመረጋጋት፣ በግላዊነት፣ ለድብርት የተጋለጡ እንዲሆኑ ያደርጋልና የሚል ትንታኔ ነው ያስቀመጡት- አጥኝዎቹ::

ከወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው የበለጠ በቤተሰብ ውስጥ ለሚፈጠር ሁከት ስጉ የሆኑ፣ ለጉዳት፣ ከትምህርት ቤት መገለል ለመሳሰሉ መጥፎ ክስተቶች የሚጋለጡ ታዳጊዎች በዓዕምሮ ጤናቸው ላይ የረዥም ጊዜ ተፅዕኖ እንደሚፈጠርባቸውም አጥኝዋ አረጋግጠዋል። ለዚህ ደግሞ የዓዕምሮ ጤና ጉዳዮች በአብዛኛው የሚጀምሩት በአስራዎቹ እድሜ ሊሆን እንደሚችል በንድፈ ሀሳቦች መረጋገጡን ለአብነት አንስተዋል – ኘሮፌሰሯ::

በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶችም ወደ ጉልምልና ለመሸጋገር ራስን መግዛት እና ማረቅ መቻልን ግድ ይላቸዋል:: በተቃራኒው በተመሰቃቀለ ቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠረው ጭንቀት ታዳጊ ወጣቶቹ ራሳቸውን እንዲያገሉ፣ የመማር ዕድል እንዲያጡ፣ አቅመ ቢስነት እንዲሰማቸው እንደሚያደርግ ነው በማደማደሚያት የተገለፀው::

 (ታምራት ሲሳይ)

በኲር ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here