“ኮማ”ን አሸናፊው

0
152

በቻይና በ2014 እ.አ.አ በልብ ድካም አዕምሯቸውን ስተው “ኮማ” ውስጥ ለገቡት አባወራ እማወራዋ ተስፋ ባለመቁረጥ ባደረጉላቸው እንክብካቤ ከአሥር ዓመታት በኋላ መንቃታቸውን ኤንዲ  ቲቪ ድረ ገጽ  አስነብቧል::

ሱን ሆንግሺያ የተሰኙት የአንሁይ ግዛት ኗሪዋ እማ ወራ “ ኮማ” ውስጥ ለገቡ ባለቤታቸው 10 ዓመታት ተስፋ ባለመቁረጥ ባደረጉላቸው እንክብካቤ የ84 ዓመት አዛውንቱ አባወራ ከሰመመን መንቃት ችለዋል::

አዛውንቱ ከዓስር ዓመታት በኋላ በነቁበት ቅፅበት እማወራዋ ለከፈሉት መስዋዕትነት ከልብ የመነጨ ምስጋና  ማቅረባቸውንም ድረ ገጹ አስነብቧል::

የቻይና ምርኒግ ፓስት የተሰኘው ጋዜጣ የአንሁይ ግዛት ኗሪዋ ሱን ሆንግሺያ በ2014 እ.አ.አ ኮማ ውስጥ ለገቡት የ84 ዓመት ባለቤቷ  ተስፋ ባለመቁረጥ  ያደረጉላቸው  እንክብካቤ ፍሬ ማፍራቱን ነው ያስነበበው::

እማወራዋ ባለፉት ዓመታት ባለቤታቸው አንድ ቀን እንደሚነቁ አምነው ዕለት ተዕለት ባለመሰልቸት ያልተገደበ እንክብካቤ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ነው የገለጹት። ባለፉት ዓመታት ብዙ የደከሙ ቢሆንም ባለቤታቸው በመንቃታቸው ሁለት ልጆቻውን ጨምሮ ቤተሰቡ ተመልሶ ደስተኛ ህይወት እንደሚመራ እምነታቸው መሆኑንም ነው በአፅንኦት የተናገሩት::

 (ታምራት ሲሳይ)

በኲር ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here