ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
118

የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን  በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ህጋዊና ብቃት ካላቸው በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡ሎት1.ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች  ፣ሎት2. የመኪና ጎማ ግዥ፣ሎት3. የመኪና ሽቶና ተዛማጅ እቃዎች፣ሎት4.የመኪና ታፕሰሪ እና ተዛማጅ ስራዎች፣ሎት5.የፈርኒቸር እና ተዛማጅ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ  የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ዋና መ/ቤት አድራሻው ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 05 /የገቢዎችና ጉምሩክ ቢሮ/ የነበረዉ G+4 ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 412 በመምጣት የማይመለስ ብር 150.00/አንድ መቶ ሃምሳ / በመክፈል በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የግዥ መጠን ብር200,000.00/ሁለት መቶ ሺ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት  በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት ንብረቱን የሚረከበው በተጠቃሚዎች የጥራት ትክክለኛነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
  6. አሸናፊው ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10በመቶ የዉል አፈጻጸም ዋስትና /ፐርፎርማንስ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱም ሆነ ከተጠየቀዉ እስፔስፊኬሽን ዉጭ ምንም አይነት ፅሁፍ ማስፈር የለባቸውም፡፡
  8. የጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 304 ከቀኑ 4፡15 በግልጽ ይከፈታል፡፡ በ22ኛው ቀን  የስራ ቀን ካልሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ስልክ ቁጥር 058-222-00-82

አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here