ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
124

በአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ የሚገኘው Productivity Enhancement Support to The Integrated Agro-Industrial parks & Youth Employment (PESAPYE) ፕሮጀክት ሎት 1 የተለያዩ አይነት ችግኞች /ፍሎች/ ፣ ሎት 2 የተፋሰስ ልማት የግብዓት ዕቃዎች እና ሎት 3 የጋቢዮን ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ሎት 1 ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)፣ ሎት 2 ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) አና ሎት 3 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብከመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ PESAPYE ፕሮጀክት ቢሮ ቁጥር 41 በመቅረብ በነፃ የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ፊርማ እና አድራሻ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. የግምገማ ዘዴው በጠቅላላ ድምር ዋጋ /በሎት/ እንደሚሆን ታሳቢ በማድረግ ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በአንድ ኢንቨሎፕ /ፖስታ/ በማሸግ ከግንቦት 12/2016 ዓ.ም እስከ 26/2015 ዓ.ም በአብከመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ PESAPYE ፕሮጀክት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታው በ27/09/2016 ዓ.ም 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም የተጫራች ወኪሎች ባለመገኘታቸው የጨረታው መከፈት ሂደቱ አይስታጓጎልም፡፡
  10. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈጸማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  11. የማቅረቢያ ጊዜ ሎት 1 ከሰኔ 10 እስከ 25/2016 ዓ.ም እና ሎት 3 ዉል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ 10 ተከታታይ ቀናት የትራንስፖርትና ሌሎችን ሙሉ ወጭ በራሱ ሸፍኖ እስከ አዋበል ወረዳ ጣባና በለጭት ተፋሰስ ድረስ ሎት 2 ደግሞ ዉል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ 10 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ PESAPYE ፕሮጀክት ቢሮ ቁጥር 41 ድረስ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058-320-87-86 በሥራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  14. አድራሻ ቀበሌ 08 ባ/ዳር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢ.ቁ 41

የአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here