በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ማህበራዊ ልማት ኮሚሽን የባህርዳር ደሴ ሰበካ ቅ/ጽ/ቤት በአማራ ክልል ዋግኸምራ ዞኖች በአራት ወረዳዎች ማለትም አበርገሌ ፤ ሳህላ ፤ ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ እና ዝቋላ ወረዳ Agricultural Seed Activity Project (ASAP III) ከአሜሪካ ዕርዳታ ድርጅት(USAID) በCRS(Catholic Relief Service) በኩል በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በፕሮጀክት ወረዳዎች ለበልግ /ለክረምት አዝመራ ወቅት የሚሆኑ የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘሮችን ማለትም ስንዴ፣ ጤፍ፣ ማሾ እና እንቁ ዳጉሳ ዘሮችን በጨረታ ገዝቶ በማቅረብ ድጋፍ ለማድረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ማንኛውም ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳዳር ይችላሉ፡፡ ዝርዝር መስፋርት፡-
- በአማራ ክልል ወይም ከተጠቀሱት ዞኖች በአንዱ ምርጥ ዘር የማቅረብ ፈቃድ ያለው፤ ወይም በጥምረት (Joint Venture) የምርጥ ዘር እና ተዛማች አቅራቢ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም ቫት እና ቲን ተመዘጋቢ የሆኑ፡፡
- የዘሩ ጥራት በሚመለከተው ሕጋዊ አካል የተረጋገጠ (Certified) የሆኑ፡፡
- የሚገዙ የዘር አይነቶች፤ ብዛት ፣ ጥራት እና መዳረሻ ቀበሌዎች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ማገኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ዜሮ ነጥብ ዜሮ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በተጠቀሱ ወረዳዎች ወደ ሚገኙ ቀበሌዎች /ክላስተር ለማድረስ ፈቃደኛ የሆነ የቀበሌዎች /ክላስተር ዝርዝር እና ከባሕር ዳር ያላቸው ርቀት ከጨረታዉ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አቅረቢው ወይም አሸናፊው ኩፖን (voucher) ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ፡፡
- ተጫራቾች ለአንድ ወይም ለሁሉም ወረዳዎች እንዲሁም አንድ ወይም የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘሮችን ለማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ከ ግንቦት 12/2016 ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር B1 ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ፤ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ፋይናሻል እና ቴክኒካል ፤ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ ማቅረብ አለባቻው፡፡
- ጨረታው ግንቦት 12/2016 እስከ ግንቦት 21/2016 በአየር ላይ የሚቆይ እና 10፡00 የሚዝጋ ሲሆን ግንቦት በ23/2016 ከቀኑ በ8፡30 ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ማህበራዊ ልማት ኮሚሽን የባሕር ዳር ደሴ ሰበካ ቅ/ጽ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር (251)-058320-09-09 /+2519-30-41-58-74 /+2519-72-70-11-66
በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ማህበራዊ ልማት ኮሚሽን የባህርዳር ደሴ ሰበካ ቅ/ጽ/ቤት
Tel: (251)-058320-09-09
Tel: +2519-30-41-58-74
Tel: +2519-72-70-11-66
Fax: 058-320-09-08
*-1420
E-mail:acsbdr@gmail.com
Bahir Dar
ማሳሰብያ፡ የዘሩን ጥራት የሚገልጸው ማረጋገጫ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱ ዝርዝር እውነታዎችን በግልጽ ልናሳይ ይገባል፡-
- የሰብል አይነትና ዝሪያውን (Crop and variety 😉
- የበቀለበትን አከባቢ (Where the seed was grown (country);
- የዘሩን ቁጥር (መለያ) (Seed lot number 😉
- የአረም ክስታት ሁነቴ (Incidence of weed seeds 😉
- የዘር አመል የመተላለፍ መጠን (Percentage of inert matter 😉
- የብቅለት መጠን (Germination and hard seed 😉
- መርዛማ አረሞች የመብቀል መጠንና የአረሙን ዓይነት (Names and rates of noxious weed Seed occurrence (which must conform to laws of the country where the seeds are to be used
- የጥራት ደራጃ እና የብቅለት መጠን የተመሰከረበት ቀን ወር እና ዓ/ም (Date Month/year in which purity and germination tests were completed)
- ማንኛውም ዓይነት ኬሚካል ተጠቅመው እንደሆነ የኬሚካሉ ዓይነት እና ከዚህ ጋር የተያያዘ ማንኛወም የተሰጠ አስተያየት ካለ (If seed was treated, chemicals with which treated and cautionary statement if advisable)
- ጥራቱ ዬት እና በማን እንደተረጋገጠ (Where, and by whom the seed was tested, i.e., an official of, and tested in, a laboratory in (Name of Country and City), etc.)