የመሬት ሊዝ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
119

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍ/ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት የከተማ መሬት ል/አስ/ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም የመኖሪያና የሆቴል አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ ለተጫራቾች ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ፡-

  1. ከ13/09/2016 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ ለመኖሪያ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/፣ ለሆቴል 400.00 /አራት መቶ ብር/ የማይመለስ በመክፈል እና የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ሲፒኦ ሃያ አምስት በመቶ በማስያዝ በከተማ አስተዳደሩ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 76 ድረስ በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ13/09/2016 ዓ.ም እስከ 27/09/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ27/09/2016 ዓ.ም ከቀኑ በ11፡00 ይሆናል፡፡
  4. ቦታውን መጎብኘት ለምትፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ-ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው በ28/09/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 በከተማ አስተዳደሩ ግቢ ከንቲባ አዳራሽ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በስ.ቁ /058-775-1775 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 76 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፍ/ሰላም ከተማ አስ/ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here