የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተለያዩ አገልግሎት የሚዉሉ የአገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የፈለገ ሲሆን ማለትም ፡- 1ኛ ያገለገለ የመኪና ጎማ፣ 2ኛ ያገለገለ የመኪና ባትሪ፣ 3ኛ ያገለገለ የመኪና ቼርኬ፣ 4ኛ የተጠራቀሙ ቁርጥራጭ ብረቶች ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት፡ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15/አስራ አምስት/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 103 ሰነዱን በመዉሰድ መወዳደር ይቻላል::
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥናንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ሂደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል:: ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል::
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/ስፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል::ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው የሚከፈትበት 8ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡3ዐ ሰዓት ይከፈታል::
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የሚሸጡ ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን::
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 በፋክስ 058 320 7069 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::