የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሊዝ አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አግባብ መሠረት ዘጠነኛ ዙር መደበኛ የመሬት ሊዝ ጨረታ የመኖሪያና የንግድ ቦታዎችን ለተጫራቾች በጨረታ ዉድድር ለማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መጫረት የምትፈልጉ ህጋዊ አክሲዩን፣ ድርጅት፣ ሽርክና ማህበር እንዲሁም ማንኛዉም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መጫረት የሚፈልጉ ግለሰብ ፣ ማህበር ፣ አክሲዮን /ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አሥር የሥራ ቀናት ዉስጥ የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመካነ ሰላም ገ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 210 እየመጡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ በአየር ላይ የሚቆየዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን በአስረኛዉ ቀን 11፡00 ታሽጎ በ11ኛዉ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ህጋዊ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ሁኖ ለመጫረት የፈለጉትን የጨረታ ቦታ ዋጋ በካ.ሜ በአሀዝና በፊደል በመግለጽ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታዉ ሚከፈትበት ቀን በ11ኛዉ የሥራ ቀን ሲሆን በ 10ኛዉ ቀን ታሽጎ 11ኛዉ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይሆናል፡፡
- የተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ የተጫረቱበትን ቦታ ስፋት በቦታዉ የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘዉን ዉጤት አምስት በመቶ እና በላይ በዝግ ሂሳብ ማስያዝ ለተሸናፊዎች ማስያዙት የሚጠበቅባቸዉ ሲሆን ጨረታዉ ተከፍቶ አሸናፊዉ ከታወቀ /ከተለየ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን ሲሆን ለጨረታ አሸናፊዎች ደግሞ ያሸነፉበት ቦታ ቅድሚያ ሊዝ ክፍያ ስለሚከፍሉ የማይመለስ ይሆናል፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቾች ለሲፒኦ /ጨረታ ማስከበሪያ/ ያስያዙትን ብር ጨረታዉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ መዉሰድ አለባቸዉ፡፡ በተገለጸዉ የጊዜ ገደብ የማይወስዱ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ የማይመለስ ሁኖ ለከተማ አስተዳደሩ ገንዘብ ጽ/ቤት ገቢ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ቅድሚ ካስያዘዉ የጠቅላላ ሲፒኦ /የጨረታ ማስከበሪያ አምስት በመቶ ጨምሮ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 10 የሥራ ቀናት ዉስጥ የሊዝ ቅድመ ክፍያዉን በመክፈል ሊዝ ዉለታ መፈጸም አለበት፡፡ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ ዉስጥ የጨረታ ህጉን ተከትሎ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችና በስልክ ቁጥሮቻችን 0332200033 /0332201073 /0984155397 /0967526465 ደዉለዉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታዉን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡