የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/04/2016
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን/ፑል/፣ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮን ጨምሮ ለ2 ቱም መ/ቤቶች ለ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ የቢሮ ህንፃ እና ምድረ ግቢ የጽዳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ በኮንትራት ግዥ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፉ በአነስተኛና ጥቃቅን ኢተርፕራይዝ ተደራጅተዉ ከትምህርትና ስልጠና ተቋም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆነው፤
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጥቃቅን የድጋፍ ደብዳቤ በማምጣት ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 007 ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ማግኘት ወይም መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከአነስተኛና ጥቃቅን ኢተርፕራይዝ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን አስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 007 በ16 ኛው ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በ 8፡30 ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- ሁሉም ተወዳዳሪዎች በጥቃቅን የተደራጁ መሆን አለባቸው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 96 44/ 058 220 96 46 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አዲስ ከተቋቋሙት ኢንተር ፕራይዞች ውጭ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡