የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
133

በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ባንክ እና በአፈ/ተከሣሾች  1ኛ ቻላቸው አለነ ፣2ኛ ምሳየ መላኩ፣ 3ኛ የቤቴ አሳየ ወራሽ አያል ፋሪስ፣ 4ኛ አለነ ቢያድግልኝ፣ 5ኛ ቄስ መላኩ እባቡ እና 6ኛ አሳየ ቢያድግልኝ፣ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የ6ኛ አፈፃፀም ተከሳሽ የአሳየ ቢያድግልኝ የሆነውን ቤት በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ ቀበሌ 01 በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ የሙጃ እና አካባቢዋ ማህበረሰብ ህብረት ሥራ ማህበር ጽ/ቤት፣ በሰሜን ዘውድቱ ፈንቴ እና በደቡብ በላይነሽ ፈንቴ  ተዋስኖ የሚገኘው ቤት ዋጋ ግምት ብር 320,709.50 /ሦስት መቶ ሃያ  ሺህ ሰባት መቶ ዘጠኝ ብር ሃምሳ ሳንቲም/ በሃራጅ ጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያው ከግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለ30 ቀናት  አየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ወይም መግዛት የምትፈልጉ ንብረቶቹ በሚገኙበት በሙጃ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ  በመገኝት መግዛት ወይም መጫረት  የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ሃያ አምስት በመቶ ለሐራጅ ባይ  ወዲያውኑ የሚያስረክብ ሲሆን ቀሪው ክፍያ ህጉ በሚደነግገው እና የፍ/ቤቱ ችሎት በሚያዘው መሰረት ለፍርድ ባለሀብቱ አጠቃሎ የሚከፍል መሆኑን ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

የሰሜን ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here