ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
141

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና ጥበቃ መምሪያ በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ በዓባይ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ የኮበልስቶንና የባዞላ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት /ማስነጠፍ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. የሥራ ፈቃድና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ የምዝገባ ስርተፊኬት (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ከ2o15 ዓም በጀት ዓመት አስከ 2o16 ዓም ጨረታው በአየር ላይ እስከ ዋለበት ድረስ ሆኖ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ብቻ የተሳተፉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. በግንባታ የሥራ ዘርፍ ወይም ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ፈቃድ ያላቸውን ደረጃ 9 እና በላይ የሆኑትን የሚያካትት መሆን አለበት፡፡
  6. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና የቅድሚያ ክፍያ ጋራንቲ እስከ ሰላሳ በመቶ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የመጫረቻ ሰነዱ በሁለት ፖስታ ዋናና ቅጅ (ኮፒ) በማሸግ ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው በአየር ላይ የሚውልበት ለ21 የሥራ ቀናት 19/09/2016 ዓ.ም እስከ 17/10/2016 ዓ.ም ሲሆን ጨረታው የሚያበቃው በ17/10/2016 ዓ.ም 11፡30 ነው፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በ18/10/2016 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  11. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡
  13. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  14. በበለጠ ስፔስፊኬሽን ዝርዘሩን ከጨረታ ሰነዱ ማየት ይቻላል፡፡
  15. አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር አርቲማቲክ ቼክ ዝቅተኛ ዋጋ እና የመወዳደሪያ ዋጋው ቫትን ይጨምራል፡፡
  16. በጨረታ ወቅት ጨረታው ውድቅ ቢሆን ተጫራቾች የሚያወጡትን ወጭ ጤና ጣቢያው አይሸፍንም፡፡
  17. ለበለጠ መረጃ ዓባይ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 01 ወይም በስልክ ቁጥር 058 321 00 89 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የአባይ ጤና ጣቢያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here