በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለወረዳው ሴ/መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው የህንፃ መሳሪያ የፅህፈት መሳርያዎችን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን የመኪና ጎማ እንዲሁም የፃግብጂ ወረዳ ገጠር መንገድ ለሚያሰራው የመንገድ እና የድልድይ ዲዛይን ሥራን እንዲሁም የኤክስካባተር ማሽን ኪራይ በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት (መከራየት) ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-
- ከሚወዳደሩት ሥራ ጋር የተዛመደ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የተሰጣቸዉ ፈቃድ አንድ አመት የሞላዉ ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer ldentificatin Number) ያላቸዉ፡፡
- በግዥ አፈጻጸም መመሪያዉ የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ተመዝጋቢዎች ብቻ እንዲወዳደሩ ከተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች ዉጭ የግዥዉ መጠን ከ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ የእቃዎች ን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርዓት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንክ ዋስትና) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /ዋናዉን የገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ዘወትር በሥራ ስዓት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሀሳቡን በኣንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ፃ/ወ/ገንዘብ /ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 4፡30 ላይ የሚከፈት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በዚህ የጨረታ ማስታዎቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 2003 ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- በግዥ መመሪያ ቁጥር 2003 መሰረት ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቀድመው ከመለሱ የጨረታ መክፈቻ ጊዜውን ሳይጠብቅ የሚከፈት መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡