አዋሳ ሐይቅ

0
244

ሐዋሳ ሐይቅ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ሲዳማ ክልል፤  የአዋሳ ከተማ አካል ነው:: ኃይቁ 16 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዲሁም ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ስፋት አለው። በ2,708 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኘው ኃይቁ  ከፍተኛው ጥልቀቱ 10 ሜትር ይደርሳል።

በሐይቁ ዙሪያ ያሉ ደጋማ አካባቢዎች ለማገዶ እንጨት፣ ለእርሻ እና ለግጦሽ ደን መጨፍጨፉ የአፈር መሸርሸርን አስከትሏል:: ከዚህ በተጨማሪ በሐይቁ ዙሪያ አሸዋ እና ጠጠር ለማውጣት መቆፈሩ በዝናብ አፈሩ እየተጠረገ ደለሉ ወደ ኃይቁ እንዲገባ አድርጓል::

ሐይቁን ለመጠበቅ የሚደረገው ጥረት አነስተኛና የተቀናጀ ባለመሆኑ ዓሣ በማስገር እና በዙሪያው ጠብሰው በመሸጥ በሚተዳደሩ ኗሪዎች እንዲሁም በጐብኚዎች ፍሰት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፏል:: አብዛኛዎቹ የአዋሳ ከተማ ኗሪዎች በ2007 ዓ.ም የጠፋው የጨለለቃ ሐይቅ ዕጣ ፈንታ ይደርስበታል የሚል ስጋትም አድሮባቸዋል::

የአዋሳ ሐይቅ የውኃ ጥራቱ  ከጊዜ ወደ ጊዜ  እየተበላሸ መምጣቱ ነው የተብራራዉ:: ለዚህም  ወደ ኃይቅ የሚገባ ፍሳሽ እና ውጋጅ ኘላስቲክ ወ.ዘ.ተ መጠኑ መጨመር የከተማዋ ኗሪዎች ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር እንደሚያያዝ ተጠቅሷል:: በተጨማሪም በሐይቁ  ውስጥ ሚገኝ የዓሣ ሀብት አጠቃቀም ላይ ቁጥጥር  አለመደረጉ በሐይቁ ዘላቂነት ላይ ያጠላ እንከን መሆኑ ተጠቋሟል::

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ብሪሊያንት ኢትዮጵያ እና ቪዚት ሲዳማ ድረ ገፆችን ተጠቅመናል::

  (ታምራት ሲሳይ)

በኲር ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here