ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁ.001

0
134

የሰ/ወሎ ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ  ከሃምሌ 1/2016 ዓ.ም እስከ  ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ለ 1 አመት የሚቆይ ሎት1. ሰርገኛ ጤፍና የተከካ በቆሎ፣ሎት2. ፊኖ ነጭ የዳቦ ዱቄት፣ሎት 3.ምጥን ሽሮና በርበሬ እንዲሁም የባልትና ዉጤቶች የሚያቀርቡ ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. በዚሁ የስራ መስክ ለመሰማራት የተመዘገቡ፡፡
  5. በስማችዉ የታተመ ደረሰኝ ሊኖር ይገባል፡፡
  6. የሚሞላዉ ዋጋ ከብር 200‚000.00(ሁለት መቶ ሽህ ) በላይ ስለሆነ ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  7. የጨረታው ማስታወቂያ  በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ26/09/2016 እስከ 10/10/2016. ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ብቻ ነዉ፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና  1 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዩ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ከ26/09/2016 እስከ 10/10/2016 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር / በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ከቀኑ 3፡30 ድረስ ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀዉ ሣጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በዚሁ ቀን ከቀኑ 3፡30 ላይ ታሽጎ 4፡00 ላይ የጨረታው ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች ያሸነፋትን አቅርቦቶች በሙሉ በራሳቸዉ ወጭ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻ፣ ማህተም ፊርማና ሌሎችን ማስረጃዎች አሟልተዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  13. በጨረታዉ የሚቀርቡ አቅርቦቶች በሙሉ ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸዉ፡፡
  14. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የዉል ማስከበሪያ 10በመቶ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  16. የበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033-331-1240/0010 ወይም 0920784565 በመደወል ወይም በአካል ወደ ቢሮው በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰ/ወሎ ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here