በድጋሜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
132

ቁጥር 10/2016

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን  የስቱዲዩ ኤ እና የልጆች ቻናል ስቱዲዩ የኢንቴረር ስራ በግልጽ ጨረታ ዘዴ ተጯራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራት  ይፈለጋል:: ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት፡ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል::
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል::
  3. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15/አስራ አምስት/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ 300/ሶስትመቶ/ብር በመግዛት አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 103  በመዉሰድ  መወዳደር ይቻላል:: የኢንቴረር ስራዎችን ቴክኒካል እና ፋይናስ ሰነዱን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ::
  4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥናንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል::
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/ስፒኦ/፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል::ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  6. ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡3ዐ ሰዓት ይከፈታል::
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  8. የሚፈለጉትን የኢንቴረር ዲዛይን ስራዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን::
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል::
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 በፋክስ 058 320 7069 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::

       አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

   ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here