የፍ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ወጀት ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚዉል ኮብል እና ጠጠር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስራጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል::
- የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ወይም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያና ዋስትና ለሚወዳድሩበት ብር ወይም ዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የዋጋ መሙያ ሰነዳቸው ላይ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ጨረታው ከወጣበት ቀን ለአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ይውልና በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፤ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም::
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 13 75 77 87 /058 775 22 54 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የተጫረቱትን የግንባታ ቁሳቁስ አጓጉዘዉ ፍ/ሰላም ከተማ መሥሪያ ቤቱ ያዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የተጫረቱትን የግንባታ ቁሳቁስ አጓጉዘው በፍጥነት ማቅረብ መቻል አለባቸው::
- ከላይ ስለ ጨረታው ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩ በ2003 የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ::