የጨረታ ማስታወቂያ

0
150

የጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ደ/ማ/ዲ /ግጨ001/2016

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደ/ማርቆስ ዲስትሪክት  ከዚህ በታች የተገለፁትን   የከባድ መኪና መለዋወጫ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት የዕቃው ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ መዝጊያ ቀን እና  ሰዓት የጨረታ መክፈቻ ቀን እና  ሰዓት
1 የተለያዩ አይነት የከባድ መኪና መለዋወጫ ግዥ 10,000.00 ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡0 ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30
2 የተለያዩ አይነት የዘይት እና ግሪስ ግዥ 10,000.00 ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30

 

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ያላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ያላው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከሰኔ 03/2016 ዓ.ም ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ደ/ማ/ዲስትሪክት በሚገኘው ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት እቦሳ የገብያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 ስልክ ቁጥር 058 178 46 33 /058 178 12 02 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ‹‹Ethiopia Electric Utilty›› የሚል የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  7. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደ/ማርቆስ ዲስትሪክት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here