የዋድላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለደለንጋ ጤና ጣቢያ የውሃ መስመር ዝርጋታ ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች /ድርጅቶች/ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- ሕጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታው የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የተዘጋጀውን እያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይኖርባችኋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ይህ ጨረታ በ22ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ በተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፤ በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማሲያዝ ይኖርበታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ለጨረታው ላወጡት ወጭ መሥሪያ ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 033 443 01 21 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡