የጨረታ ቁጥር 11
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተለያዩ አገልግሎት የሚዉሉ የአገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የፈለገ ሲሆን ማለትም ፡-1. ያገለገለ የመኪና ጎማ, 2. ያገለገለ የመኪና ባትሪ፣ 3. ያገለገለ የመኪና ቼርኬ እና 4. ቁርጥራጭ ብረቶች፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት፡ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ አስራ አምስት ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 103 ሰነዱን በመዉሰድ መወዳደር ይቻላል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር ሂደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አምስት በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ስፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚሸጡ ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደው አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 በፋክስ 058 320 70 69 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡