ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
145

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በEU በጀት ለተሁለደሬ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ሎት 1 ማሽን /እስካቫተር/ እና  የገልባጭ መኪና ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ጎላ ብለው መነበብ መቻል አለባቸው፡፡
  5. ጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አስራ አምስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ከ 3/10/2016 ዓ.ም እስከ 18/10/2016 ዓ.ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በ18/10/2016 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል (ባይገኙም ይከፈታል)፡፡
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የሥራ ቀን የመክፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው የሚለየው በሎት /በድምር ዋጋ ነው/፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች መሥሪያ ቤቱ በጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሰረት የማቅረብ ግደታ አለበት፡፡
  11. ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  14. ስራው ሳይጠናቀቅ ወይም እቃው ንብረት ክፍል ሳይገባ ቅድሚያ ክፍያ አይከፈልም፡፡
  15. ጨረታውን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግሥት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here