የባሕር ዳር ከተማ የአካባቢ ጥበቃ፣ ፅዳትና ውበት ጽ/ቤት በ2016 በበጀት ዓመት ገንብቶ ያጠናቀቃቸውን ሁለት ፓርኮች የማስተዳደርና የገቢ ክራይን ሥራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 1ኛ፡- ለዘንባባ መናፈሻ ዝርዝር የጨረታ መስፈርቶች፡-
የቦታው መገኛ ፋሲሎ ክ/ከተማ ቀበሌ 03
- የቦታው ልዩ መጠሪያ በቀድሞው ህዳር 11 በአሁኑ ዘንባባ መናፈሻ
- የቦታ ስፋት 2.1 ሄክታር
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ በገፀ ምድር ማስዋብ ወይም በካፌ /ሬስቶራንት/ ሆቴል ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
- የጨረታው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመናፈሻው ውስጥ የሚገኙ የገቢ ማስገኛ ምንጮች፡- አንድ የአሳ ካፊና ሬስቶራንት /Fish Corner/፣ አራት ሸድ ያላቸው የቡና መሸጫ /Coffee Corner/፣ አራት የመጽሃፍ ማስቀመጫ ቦታዎች /Book Corner/፣ ለፎቶ፣ ለሰረግ፣ ለምርቃን እና የተለያዩ ዝግጅቶች የሚካሄዱበት መድረክ ያለው፣ ጌጠኛ መቀመጫ ወንበሮች፣ አንድ ፋውንቴን፣ የተለያዩ ለመዝናኛ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን የሚያስተዳድርና ግቢውን የሚከራይ፡፡
- የአንድ ሰው የመግቢያ ዋጋ ከ10.00 /አስር ብር/ ያልበለጠ የሚያስከፍል፡፡
- በመናፈሻው ውስጥ 100 /አንድ መቶ/ ጌጠኛ ወንበሮች፣ 50 /ሀምሳ/ የውሃ ማጠጫ ስፒሪንግኪለር፣ 8 /ስምንት/ ጌት ቫልቭ፣ 50 አጭር እና 17 /አስራ ሰባት/ ረዥም የመብራት እንዲሁም 10 /አስር/ የመንገድ ዳር መብራት ቢበላሹ እና ጉዳት ቢደርስባቸው ማሠራት የሚችሉ፡፡
- የተተከሉ ችግኞች እና ዘመናዊ የሆኑ ኩኩየ ሳር በየጊዜው ውሃ በማጠጣት በማረምና በመኮትኮት አጠቃላይ እንክብካቤ ማድረግ የሚችል በጎደሉት የሚተካ፣ ያለውን በተሻለ ሁኔታ የሚያስቀጥልና የሚያስውብ፣
- የውሃ ማጠጫ ፖምፕ ብልሽት ሲገጥም ማሠራት የሚችሉ፡፡
- ካሁን በፊት ፓርክ የአስተዳደረ ወይም ያለማ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል እና በሙያው ልምድ ያለው ከሌለውም ልምድ ያለው ባለሙያ መቅጠር የሚችል፡፡
- አረንጓዴ ቦታ ለማልማቱ ከሚመለከተው ተቋም የመልካም ሥራ አፈፃፀም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የሥራ ጊዜዉ ሁለት ዓመት የሚቆይ ሁኖ በየስድስት ወሩ የሚታደስ፡፡
- የጨረታ መነሻ ዋጋ 70,000.00 /ሰባ ሽህ ብር/፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁጥር 1-16 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ ነጥብ ስድስት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ ተለይቶ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/ አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 205 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ2፡30 እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 205 በ15ኛው ቀን በ11፡00 ታሽጎ በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዛወራል፡፡
- በጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል፡፡ የመጀመሪያው ሂደት /ደረጃ የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴክኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ ከፍተኛ ብር ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 205 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 16 93 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች የማይመለስ 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቸላል፡፡
- መስፈርቱን ያሟላና ከፍተኛ የብር መጠን ያሥገባ አሸናፊ ተጫራች ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡