በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ዋና ጽ/ቤት በስሙ ለተመዘገበው የመኖሪያ ቤትና ቦታ አድራሻ ደባርቅ ከተማ ቀበሌ 03 ልዮ ቦታው መድሃኒዓለም ሰፈር በእዳ ተረክቦ በስሙ ያስመዘገበውን ቤት በአዋሳኝ በምሥራቅ ቢራራ ታደሰ፣ በምዕራብ አህመድ አሊ፣ በደቡብ አስማማው ሃይሉ እና በሰሜን መንገድ የሚገኘውን 250 ካ.ሜ ቤትና ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተወዳዳሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገባቸው መሥፈርቶች፡-
- ማንኛውም ሰው የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ መወዳዳር ይችላል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለሚወዳዳሩበት የቤት ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ደባርቅ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1/ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ለግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ውስጥ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይም ያስያዙት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) ከሁለት በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተወዳዳሪዎች ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨታ ሃሳቡን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ካለው በራሳቸው ፊርማ ፓራፍ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደባርቅ ዙሪያ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ግለሰብ አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ስመ-ንብረት ዝውውር መፈፀም አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ያሸነፉበትን ገንዘብ ባይከፍል ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ወይም ከ10/10/2016 እስከ 24/10/2016 ይሆናል፡፡
- ይሁን እንጅ የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ጋዜጣው ከወጣበት በ16 ኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል ሆኖም ግን ይህ ቀን በዓል /በካላንደር/ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀን ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩበት የቤትና ቦታ ጨረታ በቀን ከ20/10/2016 እስከ 23/10/2016 በጽ/ቤቱ በኩል በአካል ቀርበው መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ሚወዳዳሩበት የቤት እና የቦታ መነሻ ዋጋ 1,900,000.00 /አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ ብር/ ሲሆን ከመነሻ ዋጋ በታች የሚሞላ ተወዳዳሪ ውድቅ ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሁነው የሚመረጡት ከተወዳዳሪዎች ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ የሞሉት መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና እራሳቻውን ማግለል አይችሉም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ይሄን ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በሥራ ሂደቱ ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርበው ወይም በሥልክ ቁጥር 058 117 00 11 ወይም 09 18 43 91 36 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡