በአፈ/ከሳሽ ህጻን ሄኖክ ወሰን ሞግዚት ኤልሻዳይ መኮነን እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ አቶ ክንዱ እውኑ፣ 2ኛ ቻይና ሬይልወይ እና 3ኛ ኦሮሚያ ኢንሹራንስ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈፃፀም ከሳሽ ያልተከፈላት ቀሪ 210,000.00 /ሁለት መቶ አስር ሺህ ብር/ ማስፈፀሚያ የሚሆን ንብረትነቱ የ2ኛ አፈ/ተከሳሽ ቻይና ሬይልወይ ኢንጅነሪንግ ቁጥር 3 ንብረት የሆነውን እና ላሊበላ ከተማ አስተዳደር መስቀል ክብራ ቀበሌ በአ/ተከሳሽ ካምፕ የሚገኝውንና ከዚህ ቀድሞ በጨረታ ከተሸጠው 844 ባለ 8 ቬርጋ ቶንድኖ ብረት ውጭ ያለውን 400 /አራት መቶ/ ባለ 8 ቬርጋ ብረታ የአንድ ብረት አማካን መነሻ ዋጋ 690 /ስድስት መቶ ዘጠና ብር/ በሃራጅ ጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም የሃራጅ ጨረታ ማስታወቂያው ከሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሀምሌ 01 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለ15 ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ሐምሌ 02 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ወይም መግዛት የምትፈልጉ በላሊበላ ከተማ መስቀል ክብራ ቀበሌ ቻይና ካምፕ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መግዛት ወይም መጫረት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ አሸናፊው የአሸነበትን ¼ ኛውን ለሃራጅ ባይ ባለሙያ ወዲያውኑ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
የሰ/ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት