የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት ለጂ+9 ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የውሀ ቀለም፣ የሴራሚክ ማጽጃ፣ መስታወት፣ ስትኮ፣ የፕላስቲክ ሲሊንግ፣ ሞራሌ እና የመሳሰሉትን የግንባታ ማቴሪያሎች በግልጽ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡- ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት ለሚችሉ ተጫራቾች በሙሉ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን መረጃዎች የሚነበብ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለሞሉት የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ መጠን ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ፖስታ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በፖስታ አሽገው ስማቸውን፤ አድራሻቸውን፣ የድርጅቱን ማህተም እና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ዋጋ መሙያ ገፅ ላይ በማስቀመጥና ድርጅቱ የሚገኝበት ቢሮ ድረስ በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት ግ/ክ/ንብ/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤ በተጨማሪም የሚገዙት እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተወዳዳሪ ዋጋ ላይ ተንተርሰው መጫረት አይችሉም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ወይም በአካል በመቅረብ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ቆይታ የሚኖረው ሲሆን በ21 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ ሕዝባዊ በዓል ወይም እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ3 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ብር አስር በመቶ በመክፈል ውል ይዞ ያሸነፉበትን እቃ በታዘዘው መሰረት አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- እቃውን የምንረከበው ጥራቱ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲሆን ጥራቱን ያልጠበቀ እቃ የሚያቀርብ ነጋዴ እቃውን የማንቀበል መሆኑን አውቆ ለሚደርሰው ኪሳራ ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- አሸናፊው የሚለየው ለእያንዳንዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደ/ቅ/ጽ/ቤት ሂደት ቢሮ ቁጥር 303 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 312 17 27 ወይም 033 111 23 87 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ በግዥ መመሪያው መሰረት በእያንዳንዱ እቃ ላይ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- 1. በዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ላይ ከተጠቀሰው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ውጭ በመሰረዝ እና በመደለዝ የራሱን ስፔስፊኬሽን የሞላ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም የሌለበት ሰነድ የሚያቀርብ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት