በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የግንባታ እቃዎችን በሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የጨረታው አይነት የግንባታ እቃዎች፤ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባቸዋል፡-
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ከተ.ቁ 1-3 የተጠየቀውን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው ጨረታው ከወጣበት ከ24/10/2016 ዓ.ም እስከ 8/11/2016 ዓ.ም ድረስ ለ15 ተከታታይ ቀን አየር ላይ ቆይታ ይኖረዋል፡፡
- ጨረታው በቀን 8/11/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 በደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 62 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጨራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 30.00 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል በደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና በሰነዱ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚታየው በሎት ስለሆነ ከጨረታ ሰነዱ ያሉ ሁሉንም እቃዎች መሞላት ይኖርባቸዋል እዲሁም የሚሞሉት የጨረታ ሰነዶች በኦርጅናል ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብረዉ መግባት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ሂ1 ጥቅል ዋጋ 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ጥሬ ገንዘብ ሆነ ቼክ አያይዞ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ጨረታውን ሆን ተብሎ ለማደናቀፍ የሚደረግ የዋጋ አሞላል ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የግንባታ እቃዎቹን ውል እንዲወስድ በተጠየቀ ጊዜ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በፍትህ ፊት ቀርቦ ውል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የግንባታ እቃዎቹን ደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል በማምጣት እስቶር የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚመጣ ፖስታ ዋጋ አይኖረውም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 117 05 12 ወይም 058 117 00 39 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል