ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
126

በውሃና ኢነርጅ ቢሮ ሥር የሚገኘው የማህበረሰብ መር የተፋጠነ የውሃ ሳኒቴሽንና ሀይጅን ፕሮጀክት /COWASH/ ሠራተኞች የኢንሹራንስ አገልግሎት /Insurance Coverage/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸውና የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የኢንሹራንስ አገልግሎት የሚያገኙ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች ስም ዝርዝር፣ እድሜና የደመወዝ መጠን /Gross Salary/ እንዲሁም የእያንዳንዳቸውን ሠራተኞች የቤተሰብ ስም ዝርዝርና እድሜ የሚገልጽ ሠንጠረዥ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በውሃና ኢነርጅ ቢሮ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የማህበረሰብ መር የተፋጠነ የውሃ ሳኒቴሽንና ሃይጅን ፕሮጀክት ኤክ/ሴክሬታሪና ካሸር ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አግልግሎት ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በፕሮጀክቱ ሕጋዊ ደረሰኝ አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ከመድረሱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቢሮ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ መዝጊያ ቀን 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ /ቅጽ/ ብቻ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  13. ፕሮጀክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 09 39 25 39 22 /09 18 78 61 46 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የማህበረሰብ መር የተፋጠነ የውሃ ሳኒቴሽንና ሀይጅን ፕሮጀክት /COWASH/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here