የኮበል ኢንዱሰትሪ አክሲዮን ማህበር በ2016 ዓ.ም ለድርጅቱ ለንግድ አገልግሎት የሚዉሉ የ2024 ሞዴል አዲስ ተሳቢ መኪና እና ለቢሮ አገልግሎት የሚሰጡ ኤሌክትሪክ መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን እየገለጽን፡-
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ግብር ከፍይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ መኪናዎችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ክጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ የማይመለስ 400.00 /አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ከድርጅቱ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ማቴሪያል ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በተለያየ ፖስታ ቅጅና አርጅናል በማለት በጥንቃቄ በማሸግ የኮበል ኢንዱሰትሪ አክሲዮን ማህበር በተዘጋጃው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጉልም፡፡
- ሌሎች በማስታወቂያ ያልተገለፁ ካሉ በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኮበል ኢንዱሰትሪ አክሲዮን ማህበር በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 058 218 04 46 /058 218 06 11 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የኮበል ኢንዱሰትሪ አክሲዮን ማህበር