የመቄት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለመቄት ወረዳ እንስሳት ሃብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት በተዘዋዋሪ ፈንድ በጀት ለእንስሳት ህክምና አገልግሎት የሚውል መድኃኒት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የሙያ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ግዥው ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ቀጣይ ባሉት የሥራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችል፤ ኮፒ ባለማድረጉ ጨረታውን ውድቅ አያደርገውም::
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ከ24/10/2016 ዓ.ም እስከ 8/11/2016 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ09/11/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሰለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት/ግ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ የማመለስ 100.00 /አንድ በመቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ፡፡ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- የጨረታ ሰነዱ የሚገባው ግ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢ.ቁ. 13 በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር 033 211 00 91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመቄት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት