ባለ ክብረ ወሰኑ ብስክሌት

0
138

የ39 ዓመቱ ኔዘርላንዳዊ ጐልማሳ ጓደኞቿን አስተባብሮ የሰራው ርዝመቱ 60 ሜትር የተለካ ብስክሌት ለክብረወሰን መብቃቱን ዩፒ አይ ድረ ገጽ አስነብቧል::

የ39 ዓመቱ የኔዘርላንድ ዜጋ ከልጅነቱ ጀምሮ ሲያልም የነበረውን ለማሳካት ባለሙያ ጓደኞቹን አሰባስቦ ባደረገው ጥረት ስኬታማ ሆኗል:: በሁለት ሰው የሚሽከረከረው 60 ሜትር የሚረዝመው ብስክሌትም ለክብረ ወሰን መዝገብ መብቃቱ ተገልጿል::

ኢቫን ሻልክ የተባለው ጐልማሳ በሕዝባዊ ዓመታዊ ክብረ በአላት ላይ ተንሳፋፊ ቅርፆችን በመሥራት ልምዱ ይታወቃል:: ይህንኑ ልምዱን መሠረት አድርጐም በልጅነቱ  ሲያልመው የኖረውን በውስጡ የተዳፈነ ፍላጐቱን ለማሳካት ይወስናል::  ያሰበው ተሣክቶም ከፊት መሪው በአንድ ሰው፣ ከኋላ ፔዳሉ ወይም ማሽከርከሪያው 60 ሜትር ላይ በአንድ ሰው የሚዘወር ብስክሌት ሰርቶ ለእይታ አብቅቷል።

የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ታዛቢዎች ባሉበት ረዢሙ ብስክሌት በሚገባ መሽከርከሩ  እንዲረጋገጥ ይደረጋል:: በዚህም አንድ ሰው መሪውን ሌላኛው ከኋላ (ፔዳል) መርገጫውን እያሽከረከረ 60 ሜትር የሚረዝመው ብስክሌት መቶ ሜትር ርቀት እንዲጓዝ ይደረጋል::

የክብረ ወሰን መዝጋቢ ባለሙያዎች ይህንኑ በቦታው ተገኝተው አረጋግጠው ስምና ሥራውን በክብር መዝገብ ላይ አኑረዋል:: በተመሣሣይ ተሰርቶ ብልጫ ያለው እስኪቀርብ ድረስ ክብረወሰኑ በኢቫን እንደተያዘ እንደሚቆይም ልብ ይሏል::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘወትር ሰኞ የምትታተመውን የበኲር ጋዜጣን ሙሉ ፒዲኤፍ

በhttp:// www.ameco.et/Bekur

በቴሌግራም – https://t.me/bekur123 ላይ ማግኘት ይችላሉ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here